top of page

የአቡጊዳ ጨዋታ  በአርባ ሰደሶች(Dice) ላይ የታተሙ 240 የግዕዝ ፊደላትን በመጠቀም ቃላት በመስራት፣ ሆሄያትን በማዛመድ፣ በመደርደር እና በማሰባጠር ከልጆች፣ ከቤተሰብዎ፣ ወዳጆችዎ ጋር ከፈለጉም ብቻዎትን እየተዝናኑ በቀና የውድድር መንፈስ የሚጫወቷቸው ከሃያ በላይ ልዩ ልዩ አዕምሮን የሚያሰሉ ጨዋታዎችን ይዟል፡፡ ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል የጥቂቶቹን ጨዋታዎች ስያሜ እና ትዕዛዛት እነሆ ፦

የቃርሚያ ጨዋታ

ይህን ጨዋታ በግል ወይም በቡድን መጫወት ይቻላል፡፡ ጨዋታውን ከመጀመርዎ በፊት አርባውንም ሰደሶች ከዚህ ጀርባ ካሉት የመጫወቻ ሰንጠረዦች ውስጥ አንድ በአንድ በዘፈቀደ ያስቀምጡ፡፡ ጨዋታው ከቼዝ ጋር የሚመሳሰሉ ትዕዛዛት ያሉት ሲሆን አሸናፊ ለመሆን ብዙ ሰደሶችን መቃረም (እየበሉ ማከማቸት) ያስፈልጋል)፡፡ ሰደሶችን ለመብላት ጀማሪው በሁሉም አቅጣጫ የተሰሩ ቃላትን ይፈልግና ይወስዳል፡፡ ሰደሶቹን ወደ አራት አቅጣጫ በመገልበጥም ቃላት መስራት ይቻላል፡፡ ተጫዋቾች ቃላት መስራት ካልቻለ አንዷን ሰደስ ወደፈለገው አቅጣጫ ይገፋል ወይም ይገለብጣል (መዝለል አይቻልም)፡፡ ቀጣዩ ተረኛም ቃላት ሰርቶ ሰደሶችን ይቀጥላል፡፡ ሁሉም ሰደሶች ባያልቁም ተቆጥሮ ከግማሽ በላይ ሶደሶች መቃረም የቻለ የጎተራው ጌታ በመባል አሸናፊ ይሆናል፡፡

የሰለሜ ጨዋታ

የሰለሜ ጨዋታን በግል ወይ በቡድን መጫወት ይቻላል፡፡ ጨዋታውን ለመጀመር በቅድሚያ የሚሄደው ከአርባዎቹ ሰደሶች አንዷን በማንሳት ጠረጴዛ ላይ ያስቀምጣል፡፡ የሚቀጥለው ተረኛ ተጫዋች ደግሞ በሰደሱ አናት ላይ የሚታየውን ፊደል ተከትሎ ቃል ይመሰርታል፡፡ ቀጣዩ ተጫዋችም አንድ ሰደስ አንስቶ ቃል ይምመሰርታል፡፡ በዚህ መልኩ ቃላት መመስረት ያልቻሉ ተጫዋቾች እየወጡ አንድ ሰው በአሸናፊነት እስኪቀር ጨዋታው ይቀጥላል፡፡ የዚህ ጨዋታ አሸናፊ “ካዎ” የሚል ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡

የመምሬ_-ተሜ ጨዋታ

ይህ ጨዋታ ሰደሶቹ ከሳንዱቃቸው ሳይወጡ ጀማሪ ተጫዋቹ(መምሬ) ፊደላቱን በማገላበጥ ወደጎን፣ ወደላይ፤ ወደታች እና ወደ ግራ በመደርደር ለሌላኛው ተጫዋች(ተሜ) ሳያሳዩ ብዙ ቃላት በመፍጠር የተፈጠሩትን ቃላት(ተሜው) በማስተዋል እንዲለያቸው(እንዲዘልቃቸው) የመፈተን ጨዋታ ነው፡፡ ተሜው መምሬው የፈጠራቸውን ሁሉንም ቃላት ከለየ በተራው መምሬ ሆኖ አዲስ የቃላት ድርድሮሽ (cross-word) ጨዋታ ይጀምራል፡፡ ይህን ጨዋታ በቪዲዮ ኮል ወይም በፎቶ አንስቶ በመላላክ ሌላ ቦታ፣ ወይም አገር ካለ ወዳጅ ጋርም መጫወት ይቻላል፡፡

የደቦ ጨዋታ

ይህን ጨዋታ የሚጫወቱ ተሳታፊዎች እንደ ቁጥራቸው ብዛት መጀመርያ ሰደሶቹን እኩል ይካፈላሉ፡፡ ለምሳሌ አራት ተሳታፊዎች ካሉ አስር አስር ሰደሶችን ዕኩል ይካፈላሉ፡፡ ጨዋታው እኩል ይጀምራሉ፡፡ የተሰጡትን ሰደሶች በሙሉ በመጠቃም የተለያዩ ቃላት ሰርቶ ከሁሉም መጀመርያ የጨረሰ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል፡፡ የዚህ ጨዋታ አሸናፊ የደጃአዝማችነት ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡

የሶፍ፟ዑመር ጨዋታ

ይህ ጨዋታ እንደ ቼዝ ጨዋታ ማሰላሰል የሚጠይቅ እና ረጅም ጊዜም የሚያስፈልገው ነው፡፡በማስቀደም ስምት ሰደሶች በአንድ መስመር ከታች ወደ ላይ ይደረደራሉ፡፡ መሃሉ ለሰደሶች ክፍት ተትቶ ሌሎች ስምንት ሰደሶች በትይዩ ይደረደራሉ፡፡ መሃሉ እንደ ሸለቆ ክፍት ይተዋል፡፡ ተጫዋቾች በዳር እና በዳር ካሉት ፊደላት መሃል ባለው ክፍት ቦታ ቃላት መመስረት የሚያስችላቸውን ፊደል ከሳንዱቁ አንስተው በመሰንቀር በየተራ ይጫወታሉ፡፡ ቃላት መመስረት ያልቻለ ከስምንቶቹ ሰደሶች አንዱን ይገለብጣል፡፡ ጨዋታው በዚህ መልኩ ይሄድና ቃላት መመስረት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ሲደረስ ብዙ ቃላት መስራት የቻለው ያሸንፋል፡፡ የዚህ ጨዋታ አቸናፊ አባ ገዳ የሚል ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡

የአክሱም እና ላሊበላ ጨዋታ

ሰደሶቹ በዘፈቀደ በአንድ ወይም በአራት ምሰሶ መልክ እስከተቻለ ድረስ ወደ ላይ በጥንቃቄ ይደረደራሉ፡፡ ተጫዋቾች በአራቱም አቅጣጫ እያዩ ቃላቶቹን በየተራ ይጠራሉ፡፡ ከሁሉም ተሳታፊዎች ብዙ ቃላትን የጠራ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል፡፡ የዚህ ጨዋታ አሸናፊ ፊትአውራሪ የሚል ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡

የፋሲል ግንብ ጨዋታ

ይህ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ከሰባት እስከ አስራ አራት ሰደሶች በፋሲል ግንብ አምሳያ በመሰረትነት ይደረደራሉ፡፡ ተጫዋቾች ወደላይ እና ወደ ጎን ቃላት መስራት በየሚችሉላቸውን ሰደሶች በመጠቀም በየተራ ቃላት እየሰሩ ሰደሶቹን ወደ ላይ እና ወደጎን ይከምራሉ;; ቃላት መመስረት ያልቻለው እየወጣ የሚችለው ይቀጣላል፡፡ ይህን ጨዋታ ያሸነፈ አጼ ወይም እቴጌ የሚል ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡

የዳጉ ጨዋታ

በዚህ ጨዋታ ብዙ ሰደሶችን በመጠቀም ትርጉም ያለው ረጅም አረፍተ ነገር መስራት የቻለ ተጫዋች ያሸንፋል፡፡የዚህ ጨዋታ አሸናፊ አፈ-ንጉስ ወይም ንግስት የሚል ማዕረግ ይሰጣታል፡:

የቤተሰብ አባላትን የመፈለግ ጨዋታ  በዚህ ጨዋታ ተሳታፊዎች በሽሚያ የመረጡትን ሆሄ እያነሱ የቤተሰብ አባላቶቹን  በፍጥነት ሰብስበው አንድ ላይ ይደረድራሉ፡፡ ለምሳሌ “ሀ”ን ያነሳ የሀ በተሰብ የሆኑትን ሁሂሃሄሖን ይሰበስብና ወደቀጣዩ ሆሄ ይቀጥላል፡፡ ብዙ ቤተሰቦችን የሰበሰበ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል፡፤

 

ትዕዛዛቱን በቀላሉ ለመረዳት እና የሌሎቹን ጨዋታዎች አጨዋወት ለማየት የማህበራዊ ገፆቻችንን ይከታተሉ፡፡ በተጨማሪም በመላው ዐለም ካሉ ሀበሾች ጋር የአቡጊዳ ጨዋታዎች በመጫወት እና በውድድሮቻችን በመሳተፍ ብቃትዎን ያሳዩ፤ ባለማዕረግ በመሆንም ይሸለሙ፡፡

ማሳሰብያ፡ ሳድሶቹ ከአልካሊክ የተሰሩ ሲሆን ጠንካራ እና ከባድ በመሆናቸው ህፃናት ሲጫወቱባቸው የወላጅ ክትትል ያስፈልጋል!

 

መልካም ጨዋታ!!

Abugida Games የአቡጊዳ ጨዋታ

SKU: abugida01
$29.99 Regular Price
$20.99Sale Price
    bottom of page